ስለእኛ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ቀደም ሲል የተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ፤ የውበት ፣ መናፈሻና ዘላቂ ማረፊያ ልማት አስተዳደር ቢሮ ተብሎ ሲጠራ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት በ2001፣ 2003 ፣ 2008 እና እና 2011 ዓ.ም መሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጥ ጥናት (BPR) በማድረግ ወደ ተግባር የገባ ሲሆን በእነዚያ ጊዜያት የተካሄዱ ጥናቶችን ተግባራዊ በማድረግ ወጪ ቆጣቢ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ስራዎችን በመስራት ከተማዋ በኢትዮጵያና በአፍሪካ መዲናነቷ እንዲሁም በበርካታ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫነቷ ሊኖራት የሚገባውን የአረንጓዴ ልማትና የውበት ደረጃ ላይ እንድትገኝ ለማድረግ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ቢሮው ከተማዋን ሊመጥን የሚችልና እያደገ የመጣውን የህብረተሰቡ የከተማ ውበት ፣ አረንጓዴ ልማትና መዝናኛ ቦታዎች ፍላጎት ማሟላት ባለመቻሉና እንዲሁም የተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች የተፈጥሮ ፀጋዎች በሚጠበቀው ልክ በማልማት ለከተማዋ የገጽታ ግንባታ ተገቢውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዲችሉ ማድረግ ስላልተቻለ በአዋጅ ቁጥር 62/2010 የተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማት ቢሮ በሚል እንዲዋቀር የተደረገ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ አስፈጻሚ አካላትን እንደገና ለማዋቀር ባወጣው አዋጅ ቁጥር 64/2011 ለቢሮው ተጨማሪ ተግባራትን በመስጠት እንደገና ሲዋቀር በ2011 ዓ.ም የመሰረታዊ ስራ ሂደት በማጥናትና አደረጃጀት በመፍጠር ሲሰራ ቆይቷል፡፡

01

የተቀናጀ ዘላቂ ማረፊያ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

 መመሪያዎች ፣ ስታንዳርድና ማንዋሎችን ማዘጋጀት፤
 የዘላቂ ማረፊያ ቦታዎችን መልሶ ማልማት፤ማስዋብ እና ማስተዳደር፤
 በዘላቂ ማረፊያ ቦታዎች የሚሠጡ አገልግሎቶችን የማሳደግና የማዘመን ስራ መስራት፤
 በቢሮው ለሚሠጡ አገልግሎቶች የአገልግሎት ክፍያ ማጥናት፤እንዲተገበር ማድረግ፤
 መደበኛ የዘላቂ ማረፊያ (ቀብር) አገልግሎት መስጠት፣
 በዘላቂ ማረፊያ የሚፈፀሙ ቀብሮችን መረጃ መያዝ፤ ማጠናቀር፤ የቀብር ምስክር ወረቀት መስጠት፤ የአፅም ዝውውር ፈቃድ መስጠት፤
 የሐይማኖት ተቋማት ዘላቂ ማረፊያ ወደ ስታንዳርድ እንዲመጡ የግንዛቤ ማስጨበጥ፣የመከታተል ስራ መስራት፤
 ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት
 የህብረተሰቡን የመጸዳጃ አገልግሎት ፍላጎት መለየት
 የመጸዳጃ ቤት ፍላጎትን መሰረት በማድረግ ጥናት አድርሮጎ ለዲዛይን ክፍል ማስተላለፍ /ተፈጻሚነቱን መከታተል
 የተገነቡ መፀዳጃ ቤቶችን ተረክቦ ማስተዳደር
 እድሳትና ጥገና እንድደረግላቸው ጥያቄ ማቅረብ፤
 የሻወር አገልግሎት መስጠት
 የአገልግሎት ክፍያዎችን መከለስና ማፀደቅ ፣ መቆጣጠር ፣ ህገወጥ ስራዎችን ይከላከላል፤
 የመፀዳጃ አገልግሎት መስጠት

02

የፕሮጀክት ቁጥጥርና ህብረተሰብ ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት

 የስራና አገልግሎት ጥራት የሚመራበትን መመሪያ፣ ስታንዳርድና ማኑዋሎችን ያዘጋጃል/እንድዘጋጁ ያደርጋል፤
 በዲዛይን መሰረት ያልለሙ የተፋሰስና አረንጓዴ ቦታዎች በህግ አግባብ ወደ ስታንዳርድ እንዲመጡ ማድረግ ወይም በህግ አግባብ እንዲወገዱ ማድረግ፤
 የአረንጓዴ ልማትና ግንባታ ስራዎችን የጥራት ደረጃ ከዲዛይንና የስራ ዝርዝር አንፃር አይቶ መከታተል፣መቆጣጠር፣መገምገም፣የአፈፃፀም ክፍተቶችን መለየት፣የማስተካከያ ርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፣
 የፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ከጊዜ ፣ ጥራትና ፋይናንስ አንፃር መገምገም ፣ ግብረ መልስ መስጠት፣
 ከደረጃ በታች ለተከናወኑ ስራዎች በህግ አግባብ ርምጃ እንድወሰድ ማድረግ፣
 አገልግሎቶች በስታንዳርዳቸው መሰረት እየተሰጡ መሆናቸውን መከታተል ፤ መቆጣጠር፤ ግብረ መልስ ግብረ መልስ መስጠት፤
 የፕሮጀክቶች አፈጻጸም በተመከለተ የሚቀርቡ የክፍያ ጥያቄዎች እንዳስፈላጊነቱ ከተሰራው ስራ ጋር በማገናዘብና በማረጋገጥ ለቢሮ ሃላፊ ወይም በቢሮ ሃላፊ ለሚወከል አካል ማቅረብ፣
 የልማት ስራዎች በተቀመጠው ስታንዳርድ፣ጥራት እና መጠን እንዲሰሩ ለማድረግ ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት መስራት፣
 ከቢሮው የስነ-ምግባር መከታተያና የህግ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት፣
 ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚረዱ መረጃዎችን ማደራጀት፤ የህብረተሰብ ተሳትፎን ማሳደግ፤...

03

የከተማ ውበት ልማትና ክትትል ዳይሬክቶሬት

 የከተማ ውበት ስታንዳርድ ፤ ማንዋልና መመሪዎችን ማዘጋጀት፤
 የከተማ ውበት አማራጮችን ማጥናት፤ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን መስራት፤
 የመሬት አቀማመጥ ውበት (landscaping) ሥራዎች በቅንጅት፤ መስራት፤የእጽዋት ልማት አይነት ስብጥር፣ አተካከልና ቅደም ተከተል ማስጠበቅ፤
 ፓርኮችን፤ የዋና ዋና መንገድ ዳርቻዎችን ፤ የድልድይ ግድግዳዎችን በጥበብ ንድፍ ስራ ማስዋብ፤
 ፓርኮችን ፤ የዋና ዋና መንገድ ዳርቻዎች ፤ ወንዝ ዳርቻዎችን በቅርጻ ቅርጾች ስራ የማስዋብ ስራ መስራት፤
 ዋና ዋና መንገድ ዳርዎችን ፤አጥሮችንና የድልድይ ግድግዳዎችን ተስማሚ ቀለም በመቀባት፤በሀረግ እፅዋት ዝርዎች የማስዋብ ስራ መስራት፤
 የከተማ ውበት የቀነሱ የህንጻ አጥሮች ቀለም እድሳትና ውበት ክትትል ማድረግ፤
 የማስታወቂያ ሰሌዳዎች አቀማመጥና የመንገድ ዳርና የህንፃ አጥሮች ውበት ማስጠበቅ፤ህገወጥ ማስታወቂያዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ማስወገድ/እንድወገድ ማድረግ፤
 በመንገድ ዳርቻዎች አደባባዮችና በህዝብ ፓርኮች ሄጅና ፔርጎላ (hedge and pergola) በስታንዳርድ መሰረት እንዲተገበሩ ማድረግ፤
 በመንገድ ዳርቻዎች ውበት የሚፈጥሩ የሰዎችን እንቅስቃሴ የማይረብሹ መቀመጫዎችን እንዲዘጋጁ ማድረግና ማስዋብ፤
 የባቡር ድልድይ ግድግዳዎች በሃረግ (Climbers) የዕፅዋት ዝርያዎች እንዲዋቡ ማድረግ፤...

04

የአረንጓዴ ቦታዎች እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት

እንክብካቤን የሚመለከቱ መመሪያዎችን ፣ ስታንዳርድና ማንዋሎችን ማዘጋጀት፤
• የግብዓት ፍላጎት መለየት ፣ መረጃ ማደራጀት ፣ ግዥ እንዲፈፀም ጥያቄ ማቅረብ፤
• የሚቀርቡ የዕፅዋት ግብዓት በአይነትና ጥራት ናሙናዎችን መገምገም፤
• የቀረቡ ግብዓቶችን ማሰራጨት ፣ አገልግሎት ላይ መዋላቸውን መከታተል፤
• የችግኝ ጣቢያዎችን ማስፋፋት፤ማፍላት፤ማባዛት፤ማሰራጨትና ማስተዳደር፣
• የአረንጓዴ ቦታዎችን ማስተዳደርና መንከባከብ፤
• በዋና ዋና እና መለስተኛ መንገዶች ግራና ቀኝ ዳርቻዎች፤አካፋዮችና አደባባዮች በመንገዶች መንከባከብና ማስተዳደር፤
• በመንገዶች አካፋይና ዳርቻ የደረቁና የትራፊክ እይታ የሚጋርዱትን እፅዋት ማስወገድ፤ ያደጉ ቁጥቋጦዎችን ፣ የዛፍ ቅርንጫፎችን መቀነስና መመልመል፤
• ለባለድርሻ አካላት የአረንጓዴ ቦታዎች የእንክብካቤና የአገልግሎት ፈቃድ መስጠት ፣ መከታተልና መቆጣጠር፤
• የአረንጓዴ ቦታዎች የእፅዋት በሽታና ተባይ እንዳይጠቁ መከላከል ፣ መቆጣጠር፤
• የአረንጓዴ መሰረት ልማትን ማሻሻል/እድሳት (Renovation) ስራ መስራት፤እንዲሰሩ ማድረግ፤
• የገፅ ምድር ውሃ ለአረንጓዴ ቦታ እንክብካቤ እንዲውል መስራት፤

05

ዲዛይን ዝግጅትና ግንባታ ክንውን ዳይሬክቶሬት

 በተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ለሚሰሩ የልማት ስራዎች የዲዛይን ስታንዳርድና ማንዋሎችን ማዘጋጀት፤
 በመዋቅራዊ ፕላኑ ለአረንጓዴ ቦታነት የተመላከቱ ቦታዎችን መረጃ ማደራጀት፤
 የተፋሰስ እና አረንጓዴ አካባቢዎች ወሰንና ይዞታ ማስከበር፤
 የወሰን ችግር ያለባቸው የአረንጓዴ ቦታዎችን መለየት፤
 የወሰን ችግሮች ያለባቸው እንዲፈቱ ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ማቅረብና ተከታትሎ ማስፈፀም፤
 የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ጥያቄ ማቅረብ፤ተከታትሎ ካርታ መረከብ፤
 የተፋሰስና አረንጓዴ ልማት ዝርዝር የፕሮጀክቶች ጥናትን መነሻ በማድረግ ትንተና መስራት፤
 ቢጋር ማዘጋጀት
 የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀት
 የቅየሳ መረጃ መሰብሰብ
 የአፈር ምርመራ ማካሄድ
 የገፀ-ምድር (Landscape) ዲዛይን ማዘጋጀት ፣ እንዲዘጋጅ ማድረግ፤
 በአልሚዎችና አማካሪ ድርጅቶች ተዘጋጅተው የሚቀርቡ ዲዛይኖችን ገምግሞ ምላሽ /ግብረ-መልስ/ መስጠት፣
 ግንባታዎችን ማከናወን
 የአረንጓዴ ቦታዎችን ፣ የተፋሰስና ወንዝና ወንዝ ዳርቻ ፣ ዘላቂ ማረፊያ ቦታዎችን ፣ የህዝብ መጸዳጃ ቤቶችን ዲዛይን ማዘጋጀት ፣መገንባትና ማስረከብ/ማስተላለፍ፤
 በበጎ ፈቃድ አልሚዎች እና ባለሀብቶች የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን፣መከታተልና መቆጣጠር፤
 ለገፀ-ምድር ውሃ ማሰባሰብ ዲዛይን ማዘጋጀትና መገንባት፤
 የግንባታ ስራዎችን መከታተልና መቆጣጠር፣
 በሶስተኛ ወገን ጉዳት የደረሰባቸውን የአረንጓዴ መሰረተ-ልማቶች የዋጋ ግምት ማውጣት
 ክፍያ መርምሮ ማረጋገጥ ፤ የክፍያ ሰርተፍኬት ማዘጋጀት፤
 ግንባታዎች ሲጠናቀቁ ርክክብ መፈፀም
 የለሙ ፓርኮችን ለሚመለከተው አካል ማስተላለፍ
 ያረጁና የተጎዱ ግንባታዎችን ጥገናና ዕድሳት ማድረግ፤
 የውል ሰነድ ማዘጋጀት
 ውል ማስተዳደር
 የውል አለመግባባት ሲፈጠር መረጃ አደራጅቶ ለህግ ክፍል ማቅረብ፤

06

የተፋሰስና አረንጓዴ ልማት ዳይሬክቶሬት

 መመሪያዎችን ፣ ስታንዳርድና ማንዋሎችን ማዘጋጀት፤
 የግብዓት ፍላጎት መለየት ፣ መረጃ ማደራጀት ፣ ግዥ እንዲፈፀም ጥያቄ ማቅረብ፤
 አዳዲስ ለአረንጓዴ ልማት የሚያስፈልጉ ቴክኖሎጅዎችን ማቅረብ፤
 በከተማዋ የሚተከሉ የችግኝ ዝርያዎችን መለየትና ማስተዋወቅ፤
 በከተማው ማስተር ፕላን ያልተካተቱ ነገር ግን ሊካተቱ የሚገባቸውን አረንጓዴ ቦታዎችን ማጥናት/እንዲጠኑ ማድረግ፤
 አዲስ የሚለሙ አረንጓዴ ቦታዎችን መለየትና መረጃ ማደራጀት
 የአረንጓዴ ቦታዎችን ማልማት፣እንዲለሙ ማድረግ ፤
 የለሙ የህዝብ መናፈሻዎችን ማስተላለፍ፤
 ለአየር ንብረት ለውጥ ተስማሚ የሆኑ የውጭና አገር በቀል ዝርያዎችን መትከል ፣ እንዲተከሉ ማድረግ፣
 በዋና ዋና እና መለስተኛ መንገዶች ግራና ቀኝ ዳርቻዎች፤አካፋዮችና አደባባዮች በመንገዶች ዲዛይን መሰረት ማልማት፣
 ለአልሚዎች የአረንጓዴ ልማት ፈቃድ መስጠት ፣ መከታተልና መቆጣጠር፤
 በአረንጓዴ ቦታዎች ህገወጥ የመሬት ወረራና ግንባታ እንዳይፈጸም መጠበቅ፤መከላከል፣
 የአረንጓዴ መሰረት ልማትን ማሻሻል/እድሳት (Renovation) ስራ መስራት፤
 የተፋሰስና የወንዝ መረጃዎችን መሰብሰብ ፣ ማጠናቀር፣ ማደራጀት፤
 የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች መስራት፤
 የለሙ የተፋሰስ ቦታዎችን መጠበቅ፤
 በከተማው ማስተር ፕላን ያልተካተቱ ነገር ግን ሊካተቱ የሚገባቸውን የተፋሰስና ወንዝ ዳርቻ መጠበቂያ እንዲካተቱ ጥናት ማካሄድ/ማስጠናት፤
 የተፋሰስ አካባቢዎችና ወንዝና የወንዝ ዳርቻዎችን ማልማት፣ መጠበቅ፤
 የወንዝ ዳርቻዎች የዳሰሳ ጥናት ማድረግ ፣ የመፍትሄ ሃሳብ ማቅረብ
 በተፋሰስ አካባቢዎች ለሚሰሩ የልማት ስራዎች መመሪያዎች፣የልማት ስታንዳርድና ማንዋሎችን ማዘጋጀት፤
 በተፋሰስና ወንዝ ዳርቻ ልማት ለሚሳተፉ አልሚዎች የልማትና አገልግሎት ፈቃድ መስጠት፣መከታተልና መቆጣጠር፤
 በፕላኑ የተመላከቱ የደን ቦታዎችን ማልማት ፣ ማስተዳደር ፣ መጠበቅ
 የወንዝ ማስጠበቂያ (River buffer) ቦታን ማስከበርና ማስጠበቅ
 የወንዝና ወንዝ ዳርቻዎችን ማፅዳትና መጠበቅ

የቢሮ ስልጣንና ተግባር

1.

በፕላኑየተመላከቱአረንጓዴ አካባቢዎችንይለያል፤የይዞታ ማረጋገጫማስረጃሊወጣላቸው የሚችሉትን በሚመለከተው አካል በስሙ በማስመዝገብ የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያወጣል፤

2.

ተፋሰሶችን እና አረንጓዴ አካባቢዎችን ያስከብራል፤ ይጠብቃል፤ በተፋሰሶች እና በአረንጓዴ አካባቢዎች በፕላንና በዲዛይን ያልተደገፈ ልማት እንዳይካሄድ ይከላከላል፤ ተፈጽሞ ከተገኘ በሕግ መሰረት እንዲወገድ ያደርጋል፤

3.

በከተማዋ መዋቅራዊ ፕላን መሰረት የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች እና ፓርኮችን ያለማል፤ ነባርና አዲስ የለሙትን ለህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ያስተላልፋል፤

4.

የተፋሰሶችን እና የአረንጓዴ አካባቢዎችን ቅደም ተከተል በማውጣት የልማት ወይም መልሶ የማልማት ዝርዝር ፕሮጀክት ያዘጋጃል፤ የተቀናጀ የአረንጓዴ ልማት ቦታ አቀማመጥ ዲዛይን በማዘጋጀት ለፕላንና ልማት ኮሚሽን ያቀርባል፤ ሲጸድቅም ይተገብራል ወይም እንዲተገበር ያደርጋል፤

5.

የአሽከርካሪዎችን የርቀት እይታ የሚጋርዱ ወይም የደረቁ የመንገድ ዳር፣ አካፋይ እና የአደባባይ ዕጽዋት እንደአስፈላጊነቱ ያስወግዳል ወይም ይመለምላል፤

6.

የከተማውን አየር ሚዛን የሚጠብቁ እንዲሁም ለከተማው ውበትና መናፈሻ ልማት የሚውሉየእፅዋትችግኝጣቢያዎችን ያስፋፋል፤ያስተዳድራል፤ችግኞችን ለተጠቃሚዎች አግባብ ባለው ህግ መሠረት ያቀርባል፤ ...

ስራዎቻችን

  • ሁሉም
  • ኮሪደር ልማት
  • ዘላቂ ማረፊያ
  • መናፈሻዎች
  • ወንዝ ዳርቻዎች

ኮሪደር ልማት

አፍሪካ ኮንቬንሽን ኮሪደር ልማት

የአረንጓዴ መሰረተ ልማት

የአረንጓዴ መሰረተ ልማት ስራዎች እንክብካቤ ስራ

የአረንጓዴ ልማት

የአረንጓዴ ልማት ስራዎቻችን

ወንዝ ዳርቻ

የግንፍሌ የወንዝ ዳርቻ ልማት

ኮሪደር የተዋቡና የለሙ አረንጓዴ ልማት

#በከተማችን ነዋሪዎች ንቁ ተሳትፎ በኮሪደር የተዋቡና የለሙ አረንጓዴ ልማት ስራዎችን እናስቀጥላለን !! #ቦሌ ክፍል ከተማ-ቡልቡላ

አረንጓዴ መሰረተ ልማት ስራዎች

አረንጓዴ መሰረተ ልማት ስራዎች

አረንጓዴ መሰረተ ልማት ስራዎች

አረንጓዴ መሰረተ ልማት ስራዎች

Books 2

Lorem ipsum, dolor sit amet consectetur

ኮሪደር ልማት

አፍሪካ ኮንቬንሽን ኮሪደር ልማት

ኮሪደር ልማት

#ውብ አዲስ አበባ

አረንጓዴ መሰረተ ልማት ስራዎች

አረንጓዴ መሰረተ ልማት ስራዎች

አረንጓዴ መሰረተ ልማት ስራዎች

አረንጓዴ መሰረተ ልማት ስራዎች

አረንጓዴ መሰረተ ልማት ስራዎች

አረንጓዴ መሰረተ ልማት ስራዎች

ሃላፊዎች

ክቡር አቶ ግርማ ሰይፉ

የቢሮ ሃላፊ

ወ/ሮ ፀሀይ ጌታሁን

ምክትል ቢሮ ሃላፊ

ኢንጂነር እንደሻው ከተማ

ምክትል ቢሮ ሃላፊ

አቶ ታደለ አለሙ

የፅህፈት ቤት ሃላፊ

አቶ ነጋሽ አረጋ

አማካሪ

አቶ ብሩክ ኤልያስ

አማካሪ

እኛን ለማግኘት

አድራሻ

መስቀል አደባባይ ግሮቭ ጋርደን መግቢያ

ስልክ

+251 5589 55488 55

ኢሜል

urbanbueatification10@gmail.com

Loading
መልዕክቶ ተልኳል እናመሰግናለን